Mobile menu

የግብይት ዳይሬክቶሬት

የግብይት ዳይሬክቶሬት ራዕይ ተልዕኮ ተግባርና ኃላፊነት

ተልዕኮ 

 የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ የማኑፋክቸሪንግ የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘርፍ ተኮር የሆኑ የተቀናጀ የግብይት ብቃት ባልው ባለሙያ በመስጠት ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ ሥራ ማከናወን ነው

የግብይት አገልግሎት ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት

  • በመሰረታዊ ብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዓለም አቀፍ ገበያቸው እንዲረጋገጥ በጥራት ላይ የተመሰረት ግባዓትና ምርት ትስስር እንዲፈጠር ድጋፍ መስጠት የውዳቂ ብረታብረት (Scrap management) ክምችትና ስርጭት ስርዓት መዘርጋትና ማስፈጸም፣እንዲሁም የብረት ማዕድንና ተዛማጅ ማዕድናትን ጥናት ማከናወን፤
  • በመሰረታዊ ብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የተለያዩ የገበያ ጥናቶችን ማጥናት፣ የልማት መርሀግብሮችን መፈተሸና የገበያ ዳሰሳ ጥናት በማከናወን ሊለሙ የሚገባቸውን ምርቶች መለየት፣
  • የለሙ ምርቶችን ማስተዋወቅና ማስተላለፍ 
  • ለኤክስፖርት አምራች ድርጅቶች የሚፈለጉ የመለዋወጫ ዕቃዎችን አካላትንና የቴክኒክ ድጋፎችን በመለየት የደንበኞች አገልግሎት ስራ ማከናወን፣
  • በዳይሬክቶሬቱ በተሰጠው አገልግሎት ተጠቃሚዎች ያገኙትን ውጤት መገምገም ክፍተቱን መለየትና መሙላት፣
  • የግብአትና ምርት ትስስር በኢንዱስትሪዎች መካከል መፍጠር፤

የሚሰጡ አገልግሎቶች

  1. የገቢ ምርቶችን መለየትና ቀጣይነት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ እንዲመረቱ ማድረግ፣
  2. ምርት የማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ድጋፍ መስጠት፣
  3. የግብዓትና የምርት ትስስር ድጋፍ መስጠት፣
  4. የሀገር ውስጥና የውጭ ገበያ ማፈላለግ      ፣