Mobile menu

የምርት ዲዛይንና ልማት ዳይሬክቶሬት

ተልዕኮ

የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘርፍ ተኮር የሆነ የተቀናጀ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ብቃት ባለው ባለሙያ በመስጠት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪ ማድረግ ነው፡፡

ዓላማ

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ለደንበኞቹ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ የምርት ዲዛይንና ልማት አገልግሎት መስጠት ሲሆን አገልግሎቱም በምርምርና ስርጸት መርህ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ አገልግሎቱም ቅድሚያ ትኩረት ለተሰጣቸው ኢንዱስትሪዎች የሚያገለግሉና በሀገር ውስጥ አቅም ሊለሙ የሚችሉ የምርት ልማት ስራዎችን የዳሰሳ ጥናት በማከናወን ሊለሙ የሚገባቸውን ምርቶች በተመለከተ የተለዩ ቴክኖሎጂዎችንና የጥናትና ምርምር ስራዎችን፣ ዕቅድና ፕሮፖዛል በመገምገም፣በማቀድ የሰው ኃይል፣ ጥሬ ዕቃና የማምረቻ መሳሪያዎችን ኢኮኖሚያዊ በሆነ መንገድ በማቀናጀት፣ ጥራት ያለው የምርት ልማት ስራ ማከናዎንና የለሙ ምርቶችን በማስተዋወቅ ወደ ኢንዱስትሪው እንዲተላለፉና እንዲሸጋገሩ ማድረግ እና ቅድሚያ ትኩረት ለተሰጣቸው ኢንዱስትሪዎች የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት ሲሆን በዳይሬክቶሬቱ በተሰጠው አገልግሎትም ተጠቃሚዎች ያገኙትን ውጤት በመገምገም ክፍተቱን በመለየትና በማስተካከል ግልፅነት ያለውና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠትና የደንበኞችን ፍላጎት ማርካት ነው፡፡

የምርት ዲዛይንና ልማት ዳይሬክቶሬት የዓላማ ስኬቶች

    • የቴክኒክ ድጋፍ በማግኘት በምርት መቋረጥ የሚባክን ጊዜ የቀነሱ ወጪ የቆጠቡ እና ምርታማነታቸውንና ተወዳዳሪነታቸውን የጨመሩ ፋብሪካዎች
    • በጥናትና ምርምር ውጤቶች የተገኙ አዳዲስ ምርቶችና አሰራሮችን በመጠቀም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶችን ለገበያ ያቀረቡ ፋብሪካዎች