Mobile menu

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

ተልዕኮ

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ አቅምን ለማሳደግ የሚያስችል ምርምርና ጥናትን መሠረት ያደረገ የተቀናጀ የኢንቨስትመንት የግብይትና ማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ድጋፍ ለልማታዊ ባለሃብቱ በመስጠት ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ ማድረግ ነው፡፡

ራዕይ

ፈጣንና ቀጣይ የሆነ ዕድገት ያለውና በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆነ የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ በ2015 ዕውን ይሆናል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዓላማ

የኢንስቲትዩቱ ዓላማ የሀገሪቱን የብረታ ብረትና የኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ቴክኖሎጂዎች ልማትንና ሽግግርን በማፋጠን ኢንዱስትሪዎቹ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ፈጣን ልማት እንዲያስመዘግቡ ማብቃት ይሆናል፡፡

የኢንስቲትዩቱ እሴቶች

 1. ለልማታዊ ባለሀብት ስኬት እንተጋለን!
 2. ምንጊዜም ለመማርና ለለውጥ ዝግጁ ነን!
 3. ለፈጣን የቴክኖሎጂ ልማትና ተጠቃሚነት እንሰራለን!
 4. ለምርት ጥራት አስተማማኝነት እንተጋለን!
 5. ለአካባቢው ደህንነትና እንክብካቤ እንቆማለን!
 6. ለኢንዱስትሪው የሙያ ደህንነትና ለጤንነት መረጋገጥ እንሰራለን!
 7. የሰመረ ቅንጅታዊ አሰራርን እንተገብራለን!
 8. ለሴቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንሰራለን!

 

ኢንስቲትዩታችን በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፉ የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን በውጤት ተኮር ሥርዐት የተቃኘ ስትራቴጂን አዘጋጅቶ ለትግበራ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ስትራቴጂም ሶስት የትኩረት መስኮች ተለይተዋል፡፡ እነሱም፡-

 1. የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት
  •  የንዑስ ዘርፉ ልማታዊ ባለሃብቶች ለሚያካሂዱት ኢንቨስትመንት ውጤታማነት የሚረዳ ምቹ የኢንቨስትመንት ከካባቢ እንዲፈጠር ማድረግ፣
  • የፕሮጀክት ኢንጂነሪንግ ድጋፍና አገልግሎቶችን መስጠት፣
  • ወደ ማምረት የሚሸጋገሩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችና በማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ድጋፍ ማድረግ፣ 
 2. የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የማምረት አቅም ግንባታ
  • ለኢንዱስትሪው ችግር ፈቺ የሆኑ የምርምርና ስርዓት ሥራ ማከናወንና ውጤቱንም ማሸጋገር፣
  • የምርት ደረጃ የማዘጋጀትና የጥራት ፍተሻ አገልግሎት መስጠት፣
  • ዓለም አቀፍ ኢንዴክስ ላይ ሊያደርሱ የሚያስችሉ የቤንች ማርኪንግ ጥናት ማከናወንና በኢንዱስትሪዎች እንዲተገበር ማድረግ፣
  • ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ የተሸጋገሩትን አምራቾች ምርታማነት ጥራትና ተወዳዳሪነትን እንዲያሳድጉ ድጋፍ ማድረግ፡፡
 3. የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ምርቶች የገበያ ድርሻን ማስፋፋት
  • በጥቃቅን፣አነስተኛ፣መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች መካከል የተሳላጠ የግብዓትና ምርት ትስስር እንዲሁም ከፊል ኮንትራክታዊ የሽርክናና ሌሎች ቁርኝቶች እንዲኖሩ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት፣
  • የኢንዱስትሪ ምርቶችን ኤክስፖርት የሚያደርጉና ገቢ ምርቶችን ለሚተኩ ኢንዱስትሪዎች የገበያ ድርሻቸውን ማስፋት የሚያስችሉ የተሟላ ድጋፍና አገልግሎት መስጠት፣
  • የውድቅዳቂ ብረታ ብረት ክምችትና ግብይት ሥርዓት እንዲይዝ መስራት፡፡