Mobile menu

የተገልጋዮች እና የዜጎች ቻርተር

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የተገልጋዮች እና የዜጎች ቻርተር

ግንቦት 2009  ዓ.ም.

አዲስ አበባ  

ሙሉውን በፒዲኤፍ ዳውንሎድ ያድርጉ

 1. የቻርተሩ ዓላማ

  • የዚህ ቻርተር ዓላማ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች፣ የአገልግሎት ደረጃዎች፣ የተጠቃሚ መብቶችና ግዴታዎች እንዲሁም ሌሎች ሁኔታዎችን በግልጽ በማስቀመጥ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ጥራቱን የጠበቀ በማድረግ ተገልጋዩን ማርካት ነው፡፡
 2. የተቌሙ ስም

  • የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት
 3. የተቌሙ ተልዕኮ 
  • የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ አቅምን ለማሳደግ የሚያስችል ምርምርና ጥናትን መሠረት ያደረገ የተቀናጀ የኢንቨስትመንት ፣የግብይት እና የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ድጋፍ ለልማታዊ ባለሃብቱ በመስጠት  ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ ማድረግ ነው፡፡
 4. የተቌሙ ራዕይ
  • 2017  በአፍሪካ  ቀዲሚና  በአለም  አቀፍ  ደረጃ  ተወዳዳሪ  የሆነ  ቀላል  የብረታ  ብረት  እና ኢንጅነሪንግ  ኢንደስትሪ  በመገንባት፣ ለከባድ  ኢንዱስትሪዎች  ልማት  መሰረት  ተጥሎ ማየት፡፡
 5. የተቌሙ እሴቶች
  • ለልማታዊ ባለሀብቱ ስኬት እንተጋለን፣
  •  ምንጊዜም ለመማርና ለለውጥ ዝግጁ ነን፣
  •  ለፈጣን የቴክኖሎጂ ልማትና ተጠቃሚነት  እንሠራለን፣
  • ለምርት ጥራት አስተማማኝነት እንተጋለን፣
  • ለአካባቢ ደህንነትና እንክብካቤ እንቆማለን፣ 
  •  ለኢንዱስትሪው የሙያ ደህንነት እና ጤንነት መረጋገጥ እንሰራለን፣
  • የሠመረ ቅንጅታዊ አሠራርን እንተገብራለን፣
  •  ለሴቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን እንሰራለን፣
 6. የኢንስቲትዩቱ ተገልጋዮች 
  • መካከለኛና ከፍተኛ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች
  • የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት
  • የቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎችና እና የምርምር ተቋማት
  • የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ የዘርፍና የሙያ ማህበራት
  • የጨርቃ ጨርቅ፣ቆዳ፣ኬሚካል፣ስኳር፣ፋርማሲቲካልና አግሮፕሮሰሲንግ ኢንዱስተሪዎች
  • መገናኛ ብዙሃን
  • ዜጎች

ሙሉውን በፒዲኤፍ ዳውንሎድ ያድርጉ