Mobile menu

የዋና ዳይሬክተር መልዕክት

 

                        የዋና ዳይሬክተር መልዕክት


በአገራችን መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት ባወጣቸው ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በመመራት እያካሄደ ባለው የኢንዱስትሪ ልማት አቅጣጫ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ካላቸው የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው አንደኛና ዋነኛው ነው፡፡ ዘርፉ የኤክስፖርትና ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት አቅጣጫን በሚከተሉ ንዑስ ዘርፎች የተደራጀ ሲሆን የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፉ ገቢ ምርቶችን የመተካት አቅጣጫ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ተቀምጦለት ይህንኑ ተግባራዊ በማድረግ ላይ የሚገኝ ንዑስ ዘርፍ ነው፡፡


ንዑስ ዘርፉ ለሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎች ሁሉ መሠረት ነው፡፡ በሀገራችን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ታሪክ ከፍተኛ እድገት የተመዘገበውም በዚሁ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ቀድሞ በንዑስ ዘርፉ ተመዝግበው የነበሩ ውስን የመሠረታዊ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪዎች ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት በብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ንዑስ ዘርፉ በተፈጠረ ምቹ ሁኔታቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያዎች፣የአውቶቡስና የጭነት ተሽከርካሪ ተሣቢዎች ማምረቻዎች፣የኮንስትራክሽን መሣሪያ መገጣጠሚያዎች ተመስርተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ለመሠረተ ልማት ግንባታው በግብአትነት የሚያገለግሉ የቆርቆሮ፣የቶቦላሬና የአርማታ ምርት መጠንም እመርታዊ ለውጥ አሣይቷል፡፡

ከዚህም ባሻገር ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ዕውቀት በሚጠይቁት (High-tech) አካባቢ በአሁኑ ወቅት ዘጠኝ የሚሆኑ የሞባይል፣የቴሌቪዥን መገጣጠሚያዎች እና የፍሪጅ ማምረቻዎች በአዲስ መልክ የተቋቋሙ መሆኑና መለዋወጫ ዕቃዎችን በስፋት በሀገር ውስጥ የሚያመርቱና ለማምረትም በዝግጅት ላይ ያሉ ፋብሪካዎች መኖራቸውየቴክኖሎጂ ሽግግሩ ከተገመተው በላይ ፈጣን እንዲሆን አስተዋፅኦው ከፍተኛ ነው፡፡ የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪው ዘርፍ በአሁኑ ወቅት ለኤክስፖርትና ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውሉ እንደ ስኳርና ማዳበሪያ ያሉምርቶችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን በሀገር ውስጥ አቅም ለመገንባት እየተደረገ ያለው ጥረት፣ኢንዱስትሪው ከማኑፋክቸሪንግ ንዑስ ዘርፍነት ባሻገር ትልቅ የኢንዱስትሪ መሠረተ ልማት ግንባታ አካል ነው ያሰኘዋል፡፡ በሀገሪቱ በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ የባቡር ሀዲድና የኤሌክትሪክ ኃይል ግንባታ ፕሮጀክቶችና ሌሎች መሠረተ ልማቶችም ከግብአት አቅርቦት እስከ ቴክኖሎጂ ሽግግር የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪው የልማት ድርሻ ናቸው፡፡

ባጠቃላይ ባለፉት ሶስት ዓመታት ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት፣የምርት ጥራትንና ምርታማነትን ለማሳደግ፣የምርት ልማት ሥራዎችንና ቴክኒካዊ ድጋፎችን በማድረግ የግብአትና የምርት ትስስርን ለመፍጠርና የሰው ኃይሉን ለማብቃት በብረታብረትና ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በኩል በተደራጀ የልማት ሠራዊት ከፍተኛ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡ በዚህ ሂደትም በየጊዜው ባለሃብቱም ሆነ ንዑስ ዘርፉ እየገጠሙት ያሉት ችግሮች የተለያዩ ሲሆን በመፍትሄያቸውም ዙሪያ ከንዑስ ዘርፉ ባለሃብቶችና ከማህበራቸው ጋር በጋራ እየተሰራ ነው፡፡ በአሁኑ ወቀት በሰው ኃይል ልማት ዙሪያም ከቴ/ሙ/ት/ሥ እና ከሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከላት ጋር እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስርን ለመፍጠር በዋናነት ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጋር የኢንዱስትሪው ማሀበርና ኢንስቲትዩት የምክክር መድረኮችንና ጉብኝቶችን በማመቻቸት መምህራን በኢንዱስትሪው የተግባር ስልጠና እንዲወስዱ የተደረሰው መግባባት የኢንዱስትሪውን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ችግሮች ሣንይሣዊ መፍትሔ ለማስገኘት ጠቀሜታው የጎላ ከመሆኑም ባሻገር ተሞክሮውን በመቀመር ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ዩኒቨርስቲ ትስስር ስትራቴጂን ለመንደፍ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

በሌላ በኩል በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትና በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በጋራ የሚሰሩ የመለዋወጫ ልማት ሥራዎችና የላብራቶሪ ፍተሻ የጋር ሥራዎች በከፍተኛ ደረጃ ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው ሲሆን፣ለምሳሌ በህዳሴ ግድብ ላይ የመጀመሪያውን የNDT የጋራ ፍተሻ ለማከናወን ወደ ግድቡ እንቅስቃሴ መደረጉ በሀገሪቱየማምረት አቅም ብቻ ሳይሆን ውስብስብ የሆኑና እጅግ ግዙፍ የሆኑ ምርቶችን የጥራት ፍተሻ አቅም በሀገሪቱ መገንባቱን የሚያሣይ ነው፡፡

የንዑስ ዘርፉን የግብአት አቅርቦት ችግር ለመፍታትና ከፍተኛ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የብረት ማዕድን ጥናቶችን በማጠናቀርየሀገር ውስጥ የብረት ማዕድንን ለመጠቀም ከብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ ከማዕድን ሚኒስቴርና ከኢንስቲትዩታችንየተውጣጡ ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ጥናትና ተሞክሮን የመቀመር ሥራም እየተሰራ ነው፡፡

መንግስት ለንዑስ ዘርፉ የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ በመሆኑና ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች በመኖራቸው በንዑስ ዘርፉኢንቨስትመንት ለሚሳተፉ ባለሀብቶች አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ ለመስጠት ኢንስቲትዩቱ ዝግጁ መሆኑን በመግለፅ መልእክቴን በዚህ እቋጫለሁ፡፡ አመሰግናለሁ!!!