Mobile menu

በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪግ ንዑስ ዘርፍ ከ17.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው ምርት ኤክስፖርት ተደረገ

በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪግ ንዑስ ዘርፍ ምርቶች ከ17.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የበጀት ዓመቱ የሰባት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አመልክቷል፡፡

 

በበጀት ዓመቱ ከሐምሌ እስከ ጥር ወራት ባሉት ጊዜያት 18,447,000 የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ታቅዶ 17,543,362.60 የአሜሪካን ዶላር ከንዑስ ዘርፉ ምርት ማግኘት የተቻለ ሲሆን አፈጻጸሙ 95 በመቶ ነው፡፡

ከብረታብረት እናኢንጂነሪንግኢንዱስትሪ ዘርፍ የተገኘው 2,131,750.5 የአሜሪካን ዶላር  ሲሆን 15,411,612.1 ደግሞ ከኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ አምራች ድርጅቶች መሆኑንም በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡

የውጭ ምንዛሬው የተገኘው ከ10 የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች እና ከሶስት ኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ አምራች ድርጅቶች ሲሆን ከበጀት ዓመቱ የጥቅምት ወር በኋላ የውጭ ሀገር ባለሀብቶች አፈጻጸም እንዳልተካተተ በሪፖርቱ ተገልጧል፡፡

በጥር ወር ብቻ ከአገር ውስጥ ባለሀብቶች የብረታብረት እናኢንጂነሪንግ እንዲሁም ኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ አምራች ድርጅቶች 281,733.90 የአሜሪካን ዶላር መገኘቱንም ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጧል፡፡

ምርቶችም ወደ አውሮፓ፣ ኤሲያ፣ አፍሪካና አሜሪካ ሀገራት የተላኩ መሆናቸው ታውቋል፡፡