Mobile menu

በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ንዑስ ዘርፍ ኢንዱስትሪዎች ለዜጎች የሥራ ዕድል እየተፈጠረ ነው::

በኢንስቲትዩቱ የሚግ ብየዳ (MIG Welding) ስልጠና እየተሰጠ ነው

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮ ለተውጣጡ 20 ባለሙያዎች ከታህሳስ 15 ቀን 2011 ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚግ ብየዳ (MIG Welding) ስልጠና መስጠት መጀመሩን በኢንስቲትዩቱ የስልጠናና ትምህርት ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡

የስልጠናና ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያደኑ ትርፌሳ እንዳስታወቁት ኢንስቲትዩቱ ከተሰጡት ተግባርና ኃላፊነት አንዱ ለኢዱስትሪ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት የተለያዩ ስልጠናዎችን በማሰልጠን ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት መስጠት ሲሆን በዚሁ መሰረት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮ ለተውጣጡ 20 ባለሙያዎች የሚግ ብየዳ (MIG Welding) ስልጠና እየሰጠን ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮ ከፌዴራል ጥቃቅንና አነስተኛ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ሰልጣኞቹ የተመለመሉና ከባለሙያዎቹ 3ቱ ሴቶች ሲሆን ከስልጠናው በኋላም በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ለማድረግ ስልጠናው እንደሚረዳቸው ገልጸዋል፡፡

የተግባር ስልጠናው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት እንደሚካሄድ የገለጹት ዳይሬክተሩ ከተጠናቀቀ በኋላም ብቁ የሆኑ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል ብላዋል፡፡

 

በቀጣይም ስልጠናዎች በተለያዩ ክልሎች ለመስጠት እቅድ መያዙን አቶ ያደኑ አስታውቀዋል፡፡