Mobile menu

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የድሬድዋ የትስስር ቀጠና አካላትን የትስስር ስምምነት ሰነድ አፈራረመ

 

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስትትዩት የኢትዮጲያን የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪዎችን ብቁና ሁለተናዊ ሽግግር እንዲያደርጉ ድጋፍ ማድረግ ዋነኛ አላማው ነው፡፡ ለዚህም በእውቀት የበሰሉና በተግባር የተካኑ ባለሙያዎችን ማፍራት አንዱ ተግባሩ ነው፡፡ይህንንም ለማሳካት ተቋሙ ባዋቀረው አዲስ አደረጃጀት መሰረት በ2009 ዓ/ም ጀምሮ በተበታተነ ሁኔታ ይሰጥ የነበረውን ስልጠና በተደራጀ መልክ ለመስጠት የትምርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት በማቋቋም የተለያዩዩ የአጭርና የረጅም ግዜ የንድፈ ሃሳብና  የተግባር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ 

 

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የዩንቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር(University Industry linkage)የመምራት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ ዩንቨርሲቲዎችን፣ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎችን ከኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር ኢንዱስትሪዎች የምርምር ጥናት ስራዎችን ከዩንቨርሲቲ ምሁራን የሚያገኙበት፤የዩንቨርስቲ እና ቴክኒክና ሙያ መምህራን በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የተግባር ልምምድ የሚያደርጉበትና ተማሪዎችም በኢንዱስትሪዎች የተግባር ላይ ስልጠና የሚያገኙበት የትብብር ስርዓት ይዘረጋል፡፡ የዚህ ትስስር ማጠንጠኛ በማምረቻና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ያደጉ ሃገራት ቴክኖሎጂዎችን የማፈላለግ፣የመምረጥ፣የማላመድ እና የመጠቀም በሂደትም የማሻሻል ሃገራዊ አቅም መገንባት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ስድስት የዩንቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ንኡስ ቀጠናዎችን በማበጀት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ባወጣው የትምህርትና ስልጠና፣የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር የአሰራር መመሪያ መሰርት በማድረግ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የትስስሩ አካላትን ቤንኡስ ቀጠናው በማሰባሰብ የስምምነት ሰንድ እያፈራረመና በጋራ የሚሰሩበትን የስራ ግብብነት ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል፡፡

university

 

ከንኡስ የትስስሩ ቀጠናዎች የድሬዳዋ አስተዳደር የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ልማት ዘርፍ ዩኒቨርስቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር አንዱ ሲሆን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከድሬድዋ ከተማንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ጋር በመቀናጀት ባዘጋጀው መድረክ መስከረም 8/2011 ዓ/ም በድሬድዋ ከተማ ጥሪ ከተደረገላቸው አካላት የተገኙትን 9 ኢንዱስትሪዎች ፣2 ዩንቨርስቲዎችና 3 ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ጋር ውይይት በማድረግ፣ የስምምነት ሰነድ በማፋራረም በጋራ የሚሰሩበትን አሰራር ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡ ባለድርሻ አካላቱም የተለያዩ ጥያቄና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን በተለይም በጋራ ለመስራት በተደጋጋሚኛ በቅርበት እየተገናኙ መስራት፣ ከወረት ባለፈ በእቅድ ላይ ተመሰረተ ግንኙነት እንዲኖር ትኩረት ሰጥተው ያነሷቸው ጉዳዮች ሲሆኑ አንዳቸው ያላንዳቸው ተነጣጥለው የሚሰራ ባለመሆኑ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ አጠቃላይ አስተያየት በመስጠት ቃላቸውን የመግባቢያ ሰነዱ ላይ ፊርማቸውን በማስቀመጥ አረጋግጠዋል፡፡ 

 

 

በመሆኑም የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስትቲዩት በዋናነት የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ -ኢንዱስትሪ ትስስር እንዲያስተባብር በተሰጠው አገራዊ ኃላፊነት መሠረት ቀደም ሲል በጋራ በተቋቋመው ፎረም በ2009 በጀት ዓመት የተከናወኑ ዋናዋና ጉዳዮች ሪፖርት በማዳመጥ በ2010 በጀት ዓመት በሚከናወኑ ተግባራት መነሻ ዕቅድ ላይ በመወያየት ግብአት ተሰጥቷል፡፡ በተለይም በኢንዱስትሪውና በዩኒቨርሲቲው መካከል ቀጠናን መሠረት ያደረገየኢንተርንሽፕ፣ አፓረንትሽፕ፣ የምርምር እና የማማከር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎችና የተግባር ስልጠና የትስስር ፎረሙ መሠረታዊ ጉዳዮች መሆኑን ተሳታፊዎች የጋራ ግንዛቤ ይዘዋል፡፡

 

በዚህ ውይይት ላይ ስድስቱ ቀጠናዎች አብሮ መስራት የሚያስችል በዪኒቨርሲቲውና በኢንዱስትሪ መካከል የፊርማ ሥነሥርዓት በማካሄድ ውይይቱ ስኬታማ ሆኖ የተናጠናቀቀ ሲሆን የትስስር ፎረሙን የተመለከተ የቀጣይ ጊዜ አቅጣጫም በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በአቶ ወርቅነህ ደለለኝ ተሰጥቷል፡፡