Mobile menu

ፕሮጀክት እና ኢንጂነሪንግ አገልግሎት

 1. የኢንቨስትመንት መረጃ መስጠት

  • በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስፈልጉ የገበያ፣ የመሬት፣ መብራት፣ ውሃና የመሳሰሉትን መረጃዎች በማሰባሰብና በማደራጀት መስጠት፡፡
  • ኢንቨስትመንት ከባቢና ማበረታቻ በየጥናት ሀሳብ ለፖሊስ አውጪ ማቅረብ፤አፈፃፀሙን መከታተልና ሲፀድቅ ለባለሃብቱ ማስተዋወቅና መረጃ መስጠት፡፡
 2. የፕሮጀክት ፕሮፋይል ዝግጅት

  • የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ለማስፋፋት አማራጭ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን የሚመለከቱ የፕሮጀክት ፕሮፋይል ማዘጋጀትና ማሰራጨት፤
 3. የአዋጭነት ጥናት

  •  ስትራቴጂያዊ  ጠቀሜታና በዘርፉ ትስስር ጉልህ አስተዋፅኦ ላላቸው ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ሰነድ ማዘጋጀትና ማስተዋወቅ፤
  •  የአዋጭነት ጥናቶችን መገምገም
 4. በኢንቨስትምንት ሂደት ላይ ያሉትን ፕሮጀክቶች መከታተል

  •  በቅድመ ትግበራ፣ ትግበራና ማስፋፊያ ላይ ያሉትን ፕሮጀክቶች…የባንክ ፋይናንስ ብድር ና የመሰረተ ልማት አቅርቦት (መሬት፣ መብራትና ውሃ) ያለባቸውን ችግሮች በመቅረፍ ወደ ማምረት ሂደት እንዲገቡ ማገዝና የቅርብ ክትትል ማድረግ፤
  • በቅድመ ትግበራና ትግበራ ላይ ለሚገኙ ባለሀብቶች በፕሮጀክት ትግበራ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት 
 5. በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የቴክኖሎጂ መረጣ፣ ድርድር፣ ግንባታ፣ ተከላና ኮሚሽኒንግ ላይ የቴክኒክ እና የማማከር ድጋፍ ጥራቱን የጠበቀና የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት፤