Mobile menu

መጣጥፍ - የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

 

 

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና የትኩረት መስኮቹ

ከዳዊት ወ/ኢየሱስ

በሀገራችን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ግማሽ ምዕት ዓመት ያስቆጠረ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ዳሩ ግን ለበርካታ ዓመታት ለዘርፉ ትኩረት ሳይሰጠው ቆይቷል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ የነበረው የልማት እንቅስቃሴ ደካማ ነበር፡፡ ሀገሪቱም ከዘርፉ ልታገኝ የሚገባውን የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ልማት ሳታገኝ ቆይታለች፡፡

የመንግስት ለውጥ ከተደረገ በኋላ ሊያሰሩ የሚችሉና ህዝቡን በየደረጃው ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ተቀርጸው ወደ ተግባር ተገባ፡፡ ይህም ተቀብሮ ለነበረው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ትንሣኤ ሆነለት፡፡ ምክንያቱም የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂው የግል ባለሀብቱ የኢንዱስትሪው ሞተር መሆኑን በማመኑና ማንኛውም ልማታዊ ባለሀብት በዘርፉ ለመሰማራት ቢፈልግ በሩ ክፍት መሆኑን በማወጁ ነው፡፡

ሀገራችን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለምታደርገው የትራንስፎርሜሽን ጉዞ የመጀመሪያውን አምስት ዓመታት ለሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን መደላድል ፈጥሮ አልፈዋል፡፡ በመሆኑም በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ኢንዱስትሪው መሪነቱን እየተረከበ እንዲሄድ ለማኑፋክቸሪግ ዘርፉ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡ ትኩረት ከተሰጣቸው የማኑፋክቸሪግ ዘርፍ አንዱ ደግሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ንዑስ ዘርፍ ነው፡፡

ይህ ንዑስ ዘርፍ መሠረታዊ ብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡ የመሠረታዊ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ የብረት ማዕድናትን፣ የውድቅዳቂ ብረቶችና የጠገራ ብረቶችን በመጠቀም ለኢንጂነሪንግ ንዑስ ዘርፍ ግብዓት የሚሆኑ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን የሚያካትት ሲሆን በኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፉ የሚካተቱት ደግሞ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ውጤቶችን በግብዓትነት በመጠቀም የተለያዩ የኢንጂነሪንግ ምርቶችን የሚፈበርኩ ናቸው፡፡

በሌላ አገላለጽ መሠረታዊ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪዎች ከብረት ማጣራት ጀምሮ የተለያዩ መጠን ያላቸውን የመጀመሪያ ደረጃ ምርቶችንና እነዚህን ምርቶች በግብአትነት በመጠቀም ዝርግና ጥቅል ልሙጥ ብረቶችን፣ የተለያዩ ቅርፅ ያላቸው ድፍንና ክፍት ረጃጅም የብረት

ምርቶችን፣ ሽቦዎችን፣ የሽቦ ገመዶችን፣ ቆርቆሮዎችንና ምስማሮችን የማቅለጥ፣ የማሞቅና የመዳመጥ ቴክኖሎበመጠቀም የሚያመረቱ ሲሆኢንጂነሪንግኢንዱስትሪዎችየሚባሉትደግሞየብረታብረትኢንዱስትሪውጤትንበግብአትነትበመጠቀምየተለያዩቅርፅ

ማውጫቴክኖሎጂዎችንማለትምበማቅለጥቅርፅማውጣት፣በማነጥ፣በብየዳ፣በመቀጥቀጥመሳሪያዎችንናየተለያዩመገልገያዕቃዎች

የሚያመርቱናቸው፡፡

 

ይህንዑስዘርፍለሌሎች የማኑፋክቸሪግ ዘርፎች በግብዓትነት በማገልገል ለኢንዱስትሪ መስፋፋት ከፍተኛ ሚና የሚጫዎት ሲሆን ለሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት ዕድገትም የላቀ አስተዋጽኦ አለው፡፡ በመሆኑም ካለው ሀገራዊ ፋይዳ አንጻር ንዑስ ዘርፉን የሚደግፍ መንግሥታዊተቋምመቋቋም ነበረበትናየብረታብረትኢንዱስትሪልማትኢንስቲትዩትተቋቋመ፡፡

ሀገራችንበ2017 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሠለፍ ከድህነት ጋር ከፍተኛ የሆነ ትግል እያደረገች ባለበት በዚህ ዘመን ከሁሉም ዘርፍ እምርታዊ ለውጥ እንደሚጠበቅ ይታመናል፡፡ ይህን መሠረት በማድረግም የብረታብረትኢንዱስትሪልማትኢንስቲትዩትበ2017 በአፍሪካ ቀዳሚና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ቀላል የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ በመገንባት፣ ለከባድ ኢንዱስትሪዎች ልማት መሰረት ተጥሎ ማየት የሚል ራዕይ ሰንቆ መንቀሳቀስ ቀጥሏል፡፡

ራዕዩን ዕውን ለማድረግ ታዲያ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ አቅምን ለማሳደግ የሚያስችል ምርምርና ጥናትን መሠረት ያደረገ የተቀናጀ የኢንቨስትመንት፣ የግብይትና ማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ድጋፍ ለልማታዊ ባለሀብቱ በመስጠት ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን የትኩረት መስኮች ተቀምጠዋል፡፡

ቀዳሚው የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ማስፋፋት የሚል ነው፡፡ ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በንዑስ ዘርፉ ልማት እንዲሰማሩ ሊስብ የሚችል የተሟላ የመረጃ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ለንዑስ ዘርፉ ልማታዊ ባለሀብቶች በፕሮጀክት ዝግጅትና ትግበራ የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት ወደ ማምረት የሚሸጋገሩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ማሳደግም ይጠበቃል፡፡

በዚህ ረገድ ኢንስቲትዩቱ ከ2005 በጀት ዓመት ጀምሮ አሁን እስካለንበት የ2008 በጀት ዓመት አጋማሽ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ንዑስ ዘርፍ ለሚሠማሩ ልማታዊ ባለሀብቶች ከ300 በላይ አዳዲስ የፕሮጀክት ሀሳቦችን፣ ወደ 60 የሚሆኑ የምርት መግለጫዎችን እና ከ40 በላይ የሚሆኑ የቅድመ አዋጭነት ጥናቶችን በማካሄድ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ከጥናቱም በንዑስ ዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች መረጃን በመውሰድና ጥናቱን በማሳደግና በማስፋት ተጠቃሚ በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡

ጥናቶቹ የምርት መግለጫ፣ የገበያ ጥናትና የማምረት አቅም፣ የቴክኖሎጂና ኢንጂነሪግ ሥራው (የምርት ሂደቱ፣ የሚጠቀማቸው ማሽነሪዎችና ኢኩፕመንቶች፣ የመሬት፣ የኮንስትራክሽን ሥራው እና የአካባቢው  ተፅዕኖ)፣ የጥሬ ዕቃና ሌሎች ግብዓቶች፣ የሰው ኃይልና የስልጠና ፍላጎት፣ የፋይናንስ ትንተና እና ግምገማን ያጠቃለሉ በመሆናቸው ኢንቨስት ለሚያደርጉ ልማታዊ ባለሀብቶች ጠቃሚ መረጃዎችን ያስተላልፋሉ፡፡

ጥናቶቹ ካጠነጠኑባቸው ኢንቨስትመንቶች መካከልም የኤሌክትሪክ ኬብል፣ የአርማታ ብረታ ብረት፣ የሞተር ሳይክልና መኪና መገጣጠሚያ፣ የውሃ ቱቦ ሥራና የሞባይል አክሰሰሪ መገጣጠሚያዎች ይገኙበታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በትግበራ ሂደት የሚገኙ Pሮጀክቶችን በመደገፍ ወደ ማምረት እንዲሸጋገሩ ማድረግ ሌላው ኢንስቲትዩቱ የንዑስ ዘርፉ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የሚያከናውነው ተግባር ሲሆን በያዝነው በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸም እንደሚያመለክተው ለ31 ኘሮጀክቶች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ስምንት ኘሮጀክቶች ወደ ማምረት እንዲሸጋገሩ ኢንስቲትዩቱ ድጋፍ አድርጓል፡፡

እነዚህ ወደ ማምረት የተሸጋገሩት ፕሮጀክቶች በሶስት የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዓይነቶች የተሰማሩ ሲሆን ኢንቨስትመንቶችም 3,480 ቶን የማምረት አቅም ያለው የብረታ ብረትና የቤት ዉስጥ የማብሰያ ቁሳቁስ ፋብሪካ፣ 8,65ዐ ቶን የማምረት አቅም ያለው የተሽከርካሪ መለዋወጫና ተጓዳኝ አካላት ፋብሪካ እና በዓመት በቁጥር 3ዐ,ዐዐዐ ተሽከርካሪና ሞተር ሳይክል መገጣጠም የሚችል ፋብሪካ መሆናቸውን በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡

 

ሁለተኛው የትኩረት መስክ ደግሞ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪን የማምረት አቅም ማሳደግ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢንስቲትዩቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱና ዋነኛው ንዑስ ዘርፉን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት ነው፡፡ ባለሙያ ሲበቃ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደጉም በላይ ከሌሎች ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ የሚሆን ምርትን በሚፈለገው ጥራትና ጊዜ ለማምረት ያስችላል፡፡ በመሆኑም ኢንስቲትዩቱ በቅድሚያ የስልጠና ፍላጎት የዳሰሳ ጥናት ያካሄዳል፡፡ ኢንዱስትሪዎችም በሰው ኃይላቸው የሚስተዋሉትን የተለያዩ የሙያ ክፍተቶችን በመለየት ፍላጎታቸውን ያሳውቃሉ፡፡

በዚህ የአሰራር ሥርዓትም ከ2006 በጀት ዓመት ጀምሮ ከ2 ሺ በላይ የንዑስ ዘርፉ ልዩ ልዩ ባለሙያዎችስልጠና የወሰዱ ሲሆን ስልጠናውም ኢ-አበላሽ (NDT)፣ አውቶ ካድ፣ የጥራት መፈተሻ (Quality Inspection)፣ ማሽኒግ (ሌዝ፣ ሚሊንግ እና ሲ ኤን ሲ)፣ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (Quality Management System)፣ ቤዚክ ሜታል ወርክስ፣ ካይዘን ሥራ አመራር ስርዓት፣ ሶሊድ ወርክስ ሶፍት ዌር፣ ዌልዲንግ፣ ሂት ትሪትመንትና ሌሎችንም ያጠቃልላል፡፡

ከማምረት አቅም ጋር ተያይዞ ለኮንስትራክሽን ግብዓትነት ከሚያገለግሉ ዘርፎች ጥቂቶችን እናንሳ፡- በሀገር ደረጃ 11 የሚሆኑ የአርማታ ብረታ ብረት ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ወደ 1.2 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም አላቸው፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ስድስት የሚሆኑ ከ1.8 ሚሊዮን ቶን በላይ የማምረት አቅም ያላቸው ፕሮጀክቶች ሲኖሩ ሁለቱ ፕሮጀክቶች 75,062 ቶን የማምረት አቅም ይዘው በሚቀጥለው በጀት ዓመት እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡ እነዚህ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን ምርት በመተካት ረገድ አስተዋጽዖዋቸው የጎላ ሲሆን በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መጨረሻ ላይ ለመድረስ የታቀደው የ5 ሚሊዮን ቶን መሠረታዊ ብረታ ብረት ምርት ለማሳካት አመላካች ይሆናሉ፡፡

ቆርቆሮ ሌላው ለኮንስትራክሽን ግብዓትነት ከሚያገለግሉ ዘርፎች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢንስቲትዩቱ የሚደግፋቸው ከ25 በላይ የቆርቆሮ አምራች ድርጅቶች በሀገራችን እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን ሁለት ደግሞ በፕሮጀክት ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ኢንዱስትሪዎች ታዲያ በዓመት ከ700 ሺ ቶን በላይ የማምረት አቅም አላቸው፡፡ ይህም በሀገር ውስጥ ያለውን የቆርቆሮ ፍላጎት ለማርካት የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ያሳያል፡፡

በሦስተኛ ደረጃ የትቦላሬን (Hollow Section) የማምረት አቅምን እንመለከታለን፡፡ መረጃዎች  እንደሚያሳዩት ዘጠኝ የትቦላሬ አምራች ኢንዱስትሪዎች በሀገራችን ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ድርጅቶች ታዲያ ከ269 ሺ ቶን በላይ የማምረት አቅም ያላቸው ሲሆን ከዚህም ውስጥ 50% ምርቱ ብቻ የገበያውን ፍላጎት ማርካት ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንድ ፕሮጀክት 300 ሺ ቶን የማምረት አቅም ይዞ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በመጨረሻም ኤክስፖርት የሚያደርግ ድርጅት ያለበትን የኬብል የማምረት አቅምን ስንመለከት፤ በዚህ ዘርፍ ስድስት ኢንዱስትሪዎች የሚገኙ ሲሆን ወደ 48 ሺ ቶን በዓመት የማምረት አቅም ያላቸው ናቸው፡፡ አንድ ፕሮጀክትም ከ5 ሺ ቶን በላይ ማምረት የሚችል በማምረት ሂደት ላይ ካሉ ኩባንያዎች ጋር ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ምርቶችን የገበያ ድርሻ ማስፋት ሦስተኛውና የመጨረሻው የትኩረት መስክ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ በዚህ ሥርም ገቢ ምርቶችን ለሚተኩ ኢንዱስትሪዎች የገበያ ድርሻቸውን ማስፋት የሚያስችሉ የተሟላ ድጋፍና አገልግሎት መስጠት፣ ለንዑስ ዘርፉ ምርቶች የውጭ ገበያ ማፈላለግ የሚሉትና ሌሎች ተያያዥ ተግባራት ይከናወናሉ፡፡በመሆኑም ንዑስ ዘርፉ ገቢ ምርትን ከመተካት ባለፈ ከ2006 በጀት ዓመት ጀምሮ የንዑስ ዘርፉን ምርቶች ወደ ውጪ በመላክ በውጪ ንግድ ኢንዱስትሪው ተወዳደሪ እንዲሆን ጥረት ተደርጓል፡፡

 

በዚህ መሰረት በ2006 ዓ.ም የንዑስ ዘርፉን ምርት ኤክስፖርት ማድረግ ሲጀመር ከ10 የማይበልጡ ድርጅቶች 3,189,172.99 የአሜሪካን ዶላር ገቢ ያስገኙ ሲሆን በያዝነው በጀት ዓመት የሰባት ወራት የኤክስፖርት አፈጻጸም የሚያሳየን ደግሞ ኤክስፖርት የሚያደርጉ ኢንዱስትሪዎች ቁጥር ወደ 14 ከፍ እንዳሉና ከኢንዱስትሪዎች የተገኘው የኤክስፖርት ገቢ 11,020,963.59 የአሜሪካን ዶላር መድረሱን ነው፡፡

ኤክስፖርት ከተደረጉት የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪግ ምርት ውጤቶች መካከል ሞባይል፣ የኤሌክትሪክ ኬብል፣ የግብርና መሳሪያዎች፣ ቆርቆሮ፣ ጌጣጌጦችና የቤት ቁሳቁሶች ተጠቃሽ ሲሆኑ የምርቶቹ መዳረሻ አገራትም አሜሪካ፣ ኤሽያ፣ አውሮፓና የአፍሪካ ሀገራት ናቸው፡፡ በመሆኑም ኤክስፖርት የሚያደርጉ ድርጅቶችና የተገኘው የውጭ ምንዛሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት ቢያሳይም ከዚህ በላይ መሠራት እንዳለበት ግን አመላካች ነው፡፡

በአጠቃላይ ኢንስቲትዩቱ ከእነዚህ የትኩረት መስኮቹ በመነሳት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ንዑስ ዘርፍ ድጋፍ እያደረገ ቢሆንም ሀገሪቱ ከዘርፉ የምትጠብቀውን ውጤት ለማግኘትና ኢንስቲትዩቱም ራዕዩን ለማሳካት ከፍተኛ ሥራ እንደሚጠበቅ ይታመናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ኢንዱስትሪው የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂን በመከተልና ከመልካም አስተዳደር ችግርና ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር የጸዳ አሠራርን በመዘርጋት ለሀገር ዕድገት በጋራ መረባረብ ይጠበቃል፡፡